ለደልቤና ከተማ ፈጣን ዕድገት መነሻ የሚሆኑ የግል ዘርፍ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸው ተገለፀ ።
ደልቤና :ሰኔ 18/2018 ዓ/ም በኮንሶ ዞን የኮልሜ ወረዳ ማዕከል “የደልቤና ከተማ ለኢንቬስትመንት እጅግ ተመራጭና ዘመናዊ የከተማ ፕላን ሥራዎችና የኮሪደር ልማትን በቀላሉ እውን ለማድረግ የሚቻልበት ምቹ የሆኔና በአጭር ጊዜ ውስጥ ተወንጭፎ የማደግ ተስፋ ያለው ከተማ ነው ።
በአሁኑ ጊዜ በከተማው ላይ የተለያዩ ባለሀብቶች ለከተማው ዕድገት መነሻ የሚሆኑ ፕሮጀክቶችን ቀርፀው በፍጥነት ወደ ሥራ እየገቡ ይገኛሉ ።
በከተማው ማዕከል ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው ከቅርብ ጊዜ በኋላ አገልግሎት ወደ መስጠት የሚገባው የነዳጅ ማዴያ ግንባታ ከዚህ በታች በሚታየው መልክ በሥራ ላይ ይገኛል ። ለከተማው ዕድገት የአንበሳውን ድርሻ እየተወጡ ያሉ እና ከመንግሥት ጎን ሆነው ህብረተሰቡ በቀላሉ አገልግሎት የሚያገኝባቸው የግል ዘርፎችን በከፍተኛ ተነሳሽነት እየሠሩ ከሚገኙ ባለሀብቶች አቶ ቴኖ አማንቴ የሚጠቀሱ ናቸው ።
አቶ ቴኖ አማንቴ በጣም ጎበዝና ከዘመኑ ጋር ለመራመድ የሚያስችል አመለካከት ያላቸው ባለሀብት ናቸው ፤ወደ መጠናቀቅ አካባቢ እየመጣ ያለው የነዳጅ ማዴያ ግንባታም የእሳቸው ነው ። ይህ ጅምር ለከተማው ዕድገት ወሳኝ መሠረትና ሌሎች በከተማው ኢንቨስት ለማድረግ ዕቅድ ያላቸው አካላት ቶሎ ወደ ሥራ እዲገቡ የሚያነሳሳም ነው ።

የነዳጅ ማዴያ ሥራው ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር የኮልሜ ወረዳ ማህበረሰብንና ከጎረቤት ያሉ መዋቅሮች እንዲሁም ወደ ደቡብ ኦሞ የሚያልፉ አሽከሪካሪዎች በቀላሉ አገልግሎት እንዲያገኙ ያግዛል ተብሎ ይጠበቃል ።
“ይምጡ ደልቤና ከተማ ላይ እንቨስት ያድርጉ! “
መረጃው :-የኮልሜ ወረዳ መንግሥት ኮሙኑኬሽን አገልግሎት ነው ።