በኮንሶ ዞን ኮልሜ ወረዳ ዘመናዊ የንብ ማነብ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የማርና የንብ ውጤቶችን ምርታማነት ለማሳደግና ጥራት ማሻሻል ዙሪያ በትኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ ።
ደልቤና :ሰኔ 19/2018 ዓ/ም በኮልሜ ወረዳ ግብርና ጽቤት አደጋ ሥጋት ሥራ አመራርና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት PSNP Program በካፒታል ፕሮጀክት ድጋፍ በተመረጡ በፕሮግራሙ የለሙ ተፋሰሶች ላይ የሌማት ትሩፋት ኢንቬቲቭ ሥራዎች ለማሳካት ዝግጅት ተደርጎ ወደ ሥራ የተገባ መሆኑ የኮልሜ ወረዳ አደጋ ስጋት ሥራ አመራርና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኩታዬ ኩሲያ ተናግረዋል ።
ዘመናዊ የንብ ማነብ ተግባርን ውጤታማ ለማድረግ የቦታ መረጣ ሥራዎች ተሠርተዋል ያሉት የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ፤ዘመናዊ የንብ ቀፎ ግዥን በመፈጸም አስፈላጊውን ዘመናዊ ግብዓቶችን በመጠቀም ለመላው ህብረተሰብ ተሞክሮ በሚሆን መልኩ ይሠራል ብለዋል ።
ንብ የማዛወርና ሰም የማተም ሥራ ተጀምሮ በቀጣይ በአሠራሩ ዙሪያ ሥልጠናዎችን በማዘጋጀት አርሶ አደሮችን ውጤታማ የማድረግና በቀጣይ በወረዳው ደረጃ የማር መንደሮችን እዉን ለማድረግ ይሠራል” ሲሉ በኮልሜ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራርና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት መረጃ አድርሰዉናል ።