ኮልሜ ወረዳ መንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት፣ በኮንሶ ዞን አስተዳደር ሥር የተቋቋመ መንግሥታዊ ተቋም ነው። ተቋሙ የወረዳው መዋቅር ሥራ ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶ በርካታ ያልተገለጡ እና ያልተነገረላቸው ባህላዊ እና ሰው ሠራሽ መስህቦችን ዕለት ዕለት ከማስተዋወቅ አንፃር :ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገም ይገኛል ።
በተለይ በሰንሰለታማው እና አቀበታማው የኮልሜ መልክዐ ምድር ላይ በልዩ ጥበብ የተሠሩ የእርከን ሥራዎች ሳይቀሩ ባህላይ የቤት አጥር አሠራር ፣ የድንጋይና የአፈር ቤቶች ባህላዊ የመመገቢያ ቁሳቁሶች ፣ ባህላዊ ምግቦች ፣ ባህላዊ ጭፈራዎች፣ ታሪካዊና ያልተገለጡ የቱርስት መስህቦችን መግለጥ እና ማስተዋወቅ (እንደ ኩሬታ ፣ሉካያ ” ) ዓይነት ያሉ ተራሮችን በሚገባ የማስተዋወቅ ሥራ በዘርፉ ተሠርቶ አካባቢው ይበልጥ ከሁሉም ዘንድ እንዲታወቅ ተደርጓል።
የኮልሜ ወረዳ መንግሥት ኮሙኑኬሽን ጉ/ጽ/ቤት ራዕይ ፣ዕሴቶች እና ዓላማዎች ፦
ራዕይ (Vision)
- የመንግሥትና የሕዝብን የመረጃ ፍላጎት የሚያሟላ፣ ተዓማኒ፣ ቀልጣፋ እና ውጤታማ የኮሙኒኬሽን ሥርዓት መገንባት፤ የአካባቢውን መልካም ገፅታዎችን ማስተዋወቅና ጎበኝዎችን መሳብ ፣
ተልዕኮ / ዓላማ (Mission)
- በመንግሥት ተቋማት ውስጥ ወጥነት ያለው፣ ቀልጣፋና ውጤታማ የመረጃና የኮሙኒኬሽን ሥርዓት መፍጠር፣
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አስተዳደር ሥርዓትን ማጠናከር፣
ዜጎች የመንግሥት መረጃ በቀላሉ እንዲያገኙ ማድረግ፣
ዕሴቶች
- እውነተኝነት – ትክክለኛና ተዓማኒ መረጃ ማቅረብ።
- ግልጽነት – መረጃን በግልጽና በቀላሉ ሊረዳ በሚችል መንገድ ማቅረብ።
- ተጠያቂነት – ለተሰጠ መረጃና መልዕክት ሀላፊነት መውሰድ።
- ታማኝነት – የሕዝብን አመኔታ በሚያጠናክር መልኩ መሥራት።
- ፍትሃዊነት – መረጃን ያለ አድልዎ ማቅረብ።
- ሙያዊነት – የሙያ ሥነ-ምግባርን ጠብቆ መሥራት።
- ተሳትፎና አካታችነት – የተለያዩ ማኅበረሰብ ክፍሎችን ማሳተፍ።
- ፈጣንነት – ወቅታዊና ፈጣን መረጃ ለሕዝብ ማድረስ።
- አገልግሎት ተኮርነት – የሕዝብን ፍላጎትና ጥቅም በቅድሚያ ማስቀደም።
- ፈጠራና አዳዲስ ሃሳቦችን መቀበል – ዘመናዊ የመገናኛ ዘዴዎችን መጠቀም።