አቶ ማርቆስ ማቅሾ ማንኩማ የኮልሜ ወረዳ መንግሥት ኮሙኑኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ
በኮንሶ ዞን የኮልሜ ወረዳ መዋቅር ካገኘበት እና የወረዳው ምስረታ ከተካሄደበት ጊዜ አንስቶ ፤ከጳጉሜ ወር 05/13/2015 ዓ/ም ጀምሮ “የኮልሜ ወረዳ መንግሥት ኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ” የሚል ገፅ ተከፍቶ ወደ ሥራ ገብቷል ።
የመጀመሪያው የኮልሜ ወረዳ የመንግሥት ኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው የተሾሙትና የገፁ አድሚን የሆኑት አቶ ማርቆስ ማቅሾ ማንኩማ ናቸው ። የኮልሜ ወረዳ መንግሥት ኮሙኑኬሽን ተቋም የወረዳው መዋቅር ሥራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ :በርካታ ያልተገለጡ እና ያልተነገረላቸው የነበሩ ባህላዊ እና ሰው ሠራሽ መስህቦችን ዕለት ዕለት ከማስተዋወቅ አንፃር :ከፍተኛ አስተዋፅኦን አድርጓል ፤እያደረገም ይገኛል ።
በተለይ በሰንሰለታማው እና አቀበታማው የኮልሜ ተራሮች ላይ በልዩ ጥበብ የተሠሩ የእርከን ሥራዎች ሳይቀሩ ባህላይ የቤት አጥር አሠራር ፣የድንጋይና የአፈር ቤቶች ባህላዊ የመመገቢያ ቁሳቁሶች ፣ባህላዊ ምግቦች ፣ባህላዊ ጭፈራዎች ፣ታሪካዊና ያልተገለጡ የቱርስት መስህቦችን መግለጥ እና ማስተዋወቅ (እንደ ኩሬታ ፣ሉካያ ” ) አይነት ያሉ ተራሮችን በሚገባ የማስተዋወቅ ሥራ በዘርፉ ተሠርቶ አካባቢው ይበልጥ ከሁሉም ዘንድ እንዲታወቅ ተደርጓል ።