የኮልሜ ወረዳ አስተዳደር በወረዳው ከተማ ማዕከል “ደልቤና” ላሉት የፀጥታ አካላት የትንሳኤ በዓሉን ምክንያት በማድረግ የሰንጋ በሬን አበርክቶላቸዋል ።
#ደልቤና :ሚያዚያ 02/2018 ዓ/ም የኮልሜ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ፍቅሩ ብርሃኑን ጨምሮ የወረዳው ሠላምና ፀጥታ ኃላፊ አቶ ገረሙ ካምበሎና ሌሎች የፋይናንስ ጽ/ቤት አካላት በተገኙበት :በወረዳው ማዕከል ላሉት የፀጥታ አካላት ለበዓል ዝግጅት ይሆንላቸው ዘንድ የሰንጋ በሬን አበርክቶላቸዋል ።
“የኮልሜ ወረዳ ዋና አስተዳዳዳሪ ክቡር አቶ ፍቅሩ ብርሃኑ “የፀጥታ አካላት የህብረተሰቡን ሠላም በመጠበቅና የህዝቡ ልማት ቀጣይነት እንዲኖረው አይተከ ሚናን ይጫወታሉ ፤የፀጥታ አካላት ሚናን ልተካ የሚችል ስጦታ ባይኖርም ለህዝብ ሠላም የሚከፍሉት መስዋዕትነት ትልቅ ክብርና ዝና ነው ” ሲሉ ተናግረዋል ።
“እንኳን ለስቅለትና ለትንሳኤ በዓል በሠላም አደረሰን/ አደረሳችሁ!”
መረጃው :-የኮልሜ ወረዳ የመንግሥት ኮሙኑኬሽን አገልግሎት ነው!
