በኮንሶ ዞን በኮልሜ ወረዳ በአባያና ገልገሌ ቀበሌያት የፋስካ በዓልን ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር ተካሄደ ።
#ሚያዚያ 04/2018ዓ/ም :በኮልሜ ወረዳ የአባያና የገልገሌ ቀበሌያት አመራሮችና ህብረተሰብ ድጋፍን አሰባስበው የወረዳው ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ካቢነሽ ካፒኖን ጨምሮ የወረዳው ወጣቶች በጎ ፈቃድ አመራሮች በተገኙበት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙት አቅሜ ደካሞች የአልባሳት ፣የእህልና ለዓመት በዓል የሚሆን ምግብ ነክ ድጋፎችን አድርገዋል ።
“በጎ ተግባራትን በማጠናከር ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉት አካላትን የመደገፍ ሥራን ማጠናከር ያስፈልጋል “ሲሉ የኮልሜ ወረዳ ወጣቶች በጎ አገልግሎት ኃላፊ አቶ አበል አንሲያ አሳስበዋል ።
ችግርተኞችን መደገፍ በበዓል ወቅት ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜ :ክትትል በማድረግ አስፈላጊውን ድጋፍ መስጠት የሁሉም ሰው ግንባር ቀደም ተግባር መሆን አለበትም ብለዋል ።
በወረዳው ደረጃ ከትላንት ጀምሮ በተለያዩ ቀበሌያት ድጋፉ ተጠናክሮ መቀጠሉን የገለፁት አቶ አበል ፤በተመሣሣይ ግለት በወረዳው ሁሉም ቀበሌያት ተግባሩ መቀጠል አለበት” ሲሉ ድጋፎች በተደረጉባቸው ቀበሌያት ተገኝተው መረጃ አድርሰውናል ።

